በኤጀንሲው የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት የተሰጣቸው የ174 ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሟላ መረጃ፣ የ2011 ዓ.ም ወቅታዊ የተደረገ ስለሆነ ቀጥሎ ያሉትን ማብራሪያዎች ያንብቡ፤ መረጃውን ይጠቀሙ።

በማንኛውም ተቋም የሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ስልጠናዎች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑና ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ሌሎች አግባብነት ካላቸው ፖሊሲዎች ጋር መገናዘባቸውን ለማረጋገጥ እንዲያስችል በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 351/1995 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ተቋቁሟል። ኤጀንሲው በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 መሰረት በድጋሚ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 264/2004 ዓ.ም ተቋቁሟል።
ኤጀንሲው በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት የተቋማትን ደረጃና ብቃት በመገምገም ያሉበትን ደረጃ ለህዝብ በየጊዜው ያሳውቃል። በተለይም ተማሪዎች የእውቅና ፈቃድ ባላቸው ተቋማት እንዲማሩ ወላጆችም ለልጆቻቸው ለትምህርት የሚያወጡትን ገንዘብ አግባብነት ባለው ህጋዊ ተቋምና ፕሮግራም እንዲያውሉት ለማድረግ እንዲሁም መንግሥትና ቀጣሪ ድርጅቶች የሚቀጥሯቸው ምሩቃን እውቅና ፈቃድ ካላቸው ተቋማት ሰልጥነው የወጡ ስለመሆናቸው ለማወቅ የኤጀንሲውን ድረ-ገጽ www.herqa.edu.et እና የፌስ ቡክ ገጹን መጎብኘት ያስፈልጋል።
በዚህም መሠረት በ2011 ዓ.ም በቅድመ ምረቃ በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት የተሰጣቸው ተቋማትና የትምህርት መስኮች ዝርዝር መረጃ ለተጠቃሚዎች በፒዲኤፍ እና በፒክቸር ቀርቧል። በመሆኑ ለቀጣይ የሚሻሻል መረጃ ይፋ እስኪደረግ ወላጆች ተማሪዎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ አካላት እና መላው ህብረተሰብ ቀጥሎ የተብራሩ ጉዳዮችን በማንበብ መረጃውን እንዲጠቀሙ ኤጀንሲው ያሳስባል።
*******
የእውቅና ፈቃድ ምንድን ነው?

በአዋጅ ቁጥር 650/2001 መሰረት ማንኛውም በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃግብሮች ስልጠና ለመጀመር ለደረጃው የወጣውን መመዘኛ ላሟላ ተቋም ለሶስት ዓመት ስልጠና መስጠት እንዲችል የሚሰጥ ፈቃድ ነው።
*******
የእውቅና ፈቃድ እድሳት ምንድን ነው?
በአዋጅ ቁጥር 650/2001 በእውቅና ፈቃድ ለሶስት ዓመት ሲሰራ ለነበረ ተቋም ስልጠናውን ለመቀጠል እንዲችል ለደረጃው የተቀመጠውን መመዘኛ አሟልቶ ሲገኝ ለአምስት ዓመት የሚሰጥ የፈቃድ እድሳት ነው።
*
*

አፅንኦት የሚሰጣቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው?

=የእውቅናና የእውቅና እድሳት ፈቃድ የሚሰጠው አንድን ካምፖስ መሰረት አድርጎ ነው። በመሆኑም ለአንድ ካምፖስ የተሰጠ ፈቃድ ለሌላ ካምፓስ አያገለግልም።
=ለአንድ ተቋም የተሰጠ የእውቅና ወይም የእውቅና ፈቃድ እድሳት በፈቃዱ ላይ ለተጠቀሱ የስልጠና መስኮች እና የጊዜ ገደብ ብቻ የሚያገለግል ነው።
=ማንኛውም ተቋም የእውና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄ አቅርቦ ተገምግሞ መስፈርቱን አሟልቶ የተገኘ ስለመሆኑ ኤጀንሲው በደብዳቤ ሳይገልጽለት ተማሪ መመዝገብ አይችልም፤ ይህን ሳያረጋግጡ የሚመዘገቡ ተማሪዎች ለሚደርሰው ችግር ኃላፊነቱ የተማሪዎቹና የተቋሙ ብቻ ይሆናል፤
=ተቋማት ትክክለኛውንና ሕጋዊውን መረጃ የመስጠትና በሚታይ ቦታ ላይ የመለጠፍ ግዴታ አለባቸው፤
=በመደበኛ ሞዳሊቲ ተፈቅዶለት በርቀት ወይም በርቀት ተፈውዶለት በመደበኛ ሞዳሊቲ ተቀብሎ ማስተማር ክልክል ነው፤( በመረጃው የትምህርት መስኩ ቦዳሊቲ በመደበኛ ወይም በርቀት ስለመሆኑ ተገልጿል)

=በእያንዳንዱ የትምህርት መስክ በፍቃዱ ላይ ከተገለጸው የትምህርት መስክ ደረጃ ውጪ ተቀብሎ ማስተማር አይቻልም፤ ለምሳሌ:- በመጀመሪያ ዲግሪ ፈቃድ አግኝቶ በ2ኛ ዲግሪ ተማሪ መቀበል አይችልም፤

=በርቀት ትምህርት የእውቅና እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት የሚሰጠው በርቀት ትምህርት የእውቅና አሰጣጥ መመሪያ መሰረት በዋና ማዕከል እና ተገምግመው ለተማሪዎች ተገቢውን ድጋፍ መስጠት በሚቻልባቸው ህጋዊ የቅርንጫፍ ማዕከላት ብቻ ነው።

=ማንኛውም ተቋም በኤጀንሲው ያልተፈቀደ የደረጃ ስያሜ ለራሱ በመስጠት ለማስታወቂያም ሆነ ለሌላ መጠቀም አይችልም፤ ለምሳሌ ኮሌጅ ሆኖ ሳለ ኤጀንሲው ገምግሞ ሳያረጋግጥ ራሱን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ብሎ መጥራት አይችልም፤

ማሳሰቢያ

1. መረጃው በመጀመሪያና በ2ኛ(በማስተርስ) ዲግሪ በኤጀንሲው የእውቅና ፈቃድ የተሰጣቸውን ብቻ የሚመለከት ነው፤ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መስክ የሚሰጡ ስልጠናዎች ኤጀንሲውን ስለማይመለከቱ መረጃቸውን አያካትትም፤;

2. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መሰረት ተቋቁመው በአሁኑ ወቅት በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃግብር ትምህርትና ስልጠና የሚሰጡ መንግሥታዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ከርቀት ትምህርት ውጭ) በሕግ በተደነገገው መሰረት በተሰጣቸው ኃላፊነትና ተግባር የሚሰሩ በመሆኑ ዝርዝራቸው አልተካተተም፤

3. የተቋማቱ ስም ዝርዝር የእንግሊዝኛውን ፊደል ቅደም ተከተል መሰረት ያደረገ ነው፤

4. በመረጃው የእውቅና ፈቃዳቸው ያለፈባቸው የትምህርት መስኮችም ተካተዋል፤ ይህም የእውቅና ፈቃድ ሳይታደስ ጊዜ ያለፈባቸውን የትምህርት መስኮች ያሉበትን ደረጃ አውቆ ጥንቃቄ ለማድረግ ይረዳል።


የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

 

ነገ ደግሞ ሚያዝያ 05/2011 ዓ.ም. በኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ሌላ ቀጥታ ውይይት ተዘጋጅቷል፤ ይከታተሉ፤ ደውለው አስተያየትና እና ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። ከኤጀንሲው የእውቅና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ ከሚመለከተው ባለሙያ ጋር በመሆን የሚገኙ ይሆናል።
ሰዓት፦ ከቀኑ 7:00-8:00
ስልክ፦ 0111567484 ወይም 0111562395
የተዘጋጀው በአዲስ አበባ የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ነው

 አቶ ታፈረ ቢጠና (የጥራት ኦዲትና አቅም ማጎልበት ከፍተኛ ኤክስፐርት)
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የጥራት ኦዲት ስርዓት እና አተገባበርን በተመለከተ ስልጠና በሰጡበት ወቅት
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ፤ 2011 ዓ.ም.

HERQA News

“በአዲስ አበባ እና በዙሪያው በተደረገው ድንገተኛ ፍተሸ ያለ እውቅና ፈቃድ ተማሪ መዝግቦ የሚያስተምር 27 ካምፓስ አግኝተናል፤ አንድ ካምፓስ ስንት ተማሪ ይይዛል ብላችሁ አባዙና ስንት ዜጋ ችግር ውስጥ እንደገባ ማየት ይቻላል፤.....”

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ- መጋቢት 27/2011 ዓ.ም. በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተፈጠሩ ባሉት የህግ ጥሰቶች እና የቀጣይ እርምጃዎችን በሚመለከት በተዘጋጀው መድረክ የገለጹት፤

የተጀመረው የክትትል ስራና በህገ-ወጥ ተቋማት ላይ እየተወሰደ ያለው የእርምት እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኤጀንሲው እና የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ

 

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም የከፍተኛ ትምህርት አሰራር ስርአት በማዘመን ግልጽ የሆነ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ፣ ከቴክኖሎጂ ኤንድ ኢኖቬሽን ኢኒስቲቲዩት ጋር በጋራ ቴክኖሎጂውን የማዘመን (Automat) ስራ እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት መኖሩን ገልዋል፡፡

----------------- ------------------- ------------- -----------------
መጋቢት 05 ቀን 2011 ዓ.ም. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም ፣ሚኒስር ዴኤታዎች እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እና ም/ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት ኤጀንሲው እያከናወነ ባላቸውና ባጋጠሙ ችግሮ ላይ ውይይት ተካሂዷል፤ በውይይቱ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ድንገተኛ ግምገማ መካሄዱ እና በህገ-ወጥ ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እንዲሁም እርምጃ የተወሰደባቸውን ተቋማትን ማሳወቅን ጨምሮ ሌሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።

 ለበለጠ መረጃ

 The Higher Education Relevance and Quality Assurance Agency (HERQA) has announced that Private Higher Learning Institutions in Ethiopia need to respect and work to instill the essence of the Ethiopian constitution in the public mind.

Deputy Director General of the Agency, Tamirat Motta, told Walta Information Center that Private Higher Learning Institutions in Ethiopia need to respect and aggressively work to induce the essence of the supreme law of the land in to the grass root community.

According to the Director General, it is the constitutions currently applied in the country that opened the way that enabled to Private Higher learning Institutions in the country.

 

The director said so while chairing a panel discussion organized to celebrate the 11 Nation, Nationalities and People’s Day in Harari Regional State last week.

Such Panel Discussion was organized for the first time in collaboration with Association Private Higher Learning Institutions, House of Federation and Higher Education Relevance and Quality Assurance Agency.

The director said that private higher learning institutions needs to play their part in spreading the essence of constitutionalism in the minds of the public at large since its only through abiding to the principles of the constitutions the country can ensure its peace and enhance its social and economic development goals. He argued that the institutions do not need to teach law in order to discharge its institutional responsibility.

Deputy Supreme Court Public Prosecutor of Harari Justice and Security Affairs Bureau, Meseret Alemayew, said that private higher learning institution in the country has been week in respecting and spreading the spirit of the Ethiopian constitutions while presenting a paper entitled Constitution and Higher Learning Institutions in Ethiopia to the panelist gathered at Amir Abdulahi Conference Hall.

According Meseret, participating for the first time in the Nations, Nationalities and People’s Day after a decade in an organized was is a testimony to the weakness of the private higher learning institutions.

She argued that the private higher learning institute should have been be pioneer to celebrate one of the many fruits the constitutions has been bearing over the last two decay.

Modern education started in Ethiopian at the end of 19th century. However, it has been a little over two decades since Private Higher Education has started operation in the country. Ethiopian is currently home to 106 private higher learning institutions and over 35 Public Universities.